Friday, March 9, 2012

ተሀድሶያውያኑ የቤተክህነት ጉባኤ ሲከሽፍባቸው አዳራሾችን ማሳደድ ጀምረዋል


(አንድ አድርገን የካቲት 30 2004 ዓ.ም)፡-በቤተክርስያናችን ውስጥ እንዳይሰብኩ የከለከሉት ሰዎች ከቀናት በፊት ገቢ ማሰባሰቢያ በሚል ሰበብ በጠቅላይ ቤተክህነት አዳራሽ ጉባኤ ለማድረግ ተዘጋጅተው ቤተክርስትያኗ የበላይ ሀላፊዎች መከልከላቸውን እና ጉባኤውም መደናቀፉን ዘግበን ነበር ፤ እነኚህ ሰዎች አሁን ደግሞ አዳራሾችን በመከራየት ለመሰል ተግባራቸው ሰሞኑን ሲንቀሳቀሱ ከርመዋል ፡፡ መጋቢት 2 በአትላስ ሆቴል  አካባቢ የሚገኝ  አዳራሽ ከቤተክርስትያኗ ፍቃድ ውጪ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አማኞችን  በመጥራት ምንፍቅናቻን በማር ላይ ለማቅረብ ዝግጅታቸውን አጠናቀው ጉባኤው የሚዘጋጅበትን ቀን እየጠበቁ ይገኛሉ ፡፡


 ዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ በመላው የሀገሪቱ ክፍል የአዳራሽ ጉባኤ አስፋፍተው ሰውን ከቤተክርስያን ሲያርቁ የተመለከቱት አባቶቻችን በሲኖዶስ ጉባኤ የአዳራሽ እና የሆቴሎችን ጉባኤ ከስርዓተ ቤተክርስትያን ውጪ ነው በማለት መከልከላቸው ይታወቃል ፤ ሆኖም ይህን የሚከታተል አካል በቤተክህነቱ ውስጥ ለመመልከት አልቻልንም፡፡ በልብ ህመም ውጭ ሀገር ለሚታከመው ሰው አሁንም በሆቴሎች የከለባት ጉባኤ አዘጋጅተዋል ፡፡ የትኛው የቤተክርስያን ክፍል ነው ይህን ተከታትሎ ማስቆም የሚችለው? እኛም አልገባንም ፤ የኛ ያልሆኑ አስተማሪዎች እኛን ወክለው በየትኛውም መድረክ ላይ ማስተማር አይችሉም ፤ ሆቴል እና የተለያዩ አዳራሾች የሚደረጉ ጉባኤዎች ከስርዓተ ቤተክርስያን ውጪ ናቸው ፤ በአንድ ጎን ስርዓት እያፈረሱ በሌላ ጎን ደግሞ ለእርዳታ ከሆነ ምን ችግር አለው ማለት ተገቢ አይደለም፡፡ አሁንም የኛ አቋም ወንድማችን እንዳለ ገብሬ የገቢ ማሰባሰቢያ አያድርግ የሚል አቋም የለንም ፤ ቤተክርስያንን የማይወክሉ ሰዎች ጋር ተጠግጦ ስርዓተ ቤተክርስትያን እየተጣሰ የሚደረገውን ህገ ወጥ ተግባር እንቃወማለው ፤ ስርዓት ከተጠበቀ ሁሉን በስርዓት ማድረግ ይቻላል ፡፡ ትላንት ስንት ያወዛገበውን የአዳራሽ ጉባኤ በዚች ሰበብ ምእመኑ እንዲለምደው የማድረግ የረዥም ጊዜ እቅዳቸው ነውና ነቅተን መጠበቅ ግድ ይለናል፡፡

እኛን አሁን የገደደን የብሩ ጉዳይ አይደለም ፤ ወንድማችንም አይረዳ ብለን አይደለም፡፡  ነገር ግን እነዚህ የተሐዲሶ መናፍቃን አቀንቃኞች ምን ያህል ቤተክርስቲያንን ለመበረዝ አጋጣሚዎችንና ቀዳዳዎችን እየፈለጉ ስለሆነ ነቅተን ልንጠብቃቸው ግድ ይለናል፡፡ ቤተክህነቱ ከቤተክርስትያን ውጪ የሚደረጉ ጉባኤዎችን ከቻለ በራሱ ካልቻለ ከፖሊስ ጋር በመሆን ቤተክርስትያኒቷ የማታውቃቸው መሆኑን አስገንዝቦ ማስከልከል መቻል አለበት ፤ የቤተክርስትያኒቷ ስም የሚደረጉ ህገወጥ ጉባኤዎች እንዳይደረጉ ማስቻልም አለበት ፤ ይህን ጉዳይ ስራ ብሎ የሚከታተል ክፍልም ያስፈልገዋል የሚል እምነት አለን ያለበለዚያ ሁሉም ነገር ሰዶ ማሳደድ ይሆናል  ፡፡ 



 ቀጣዩ ጉባኤ የትኛው አዳራሽ እንደሚሆን አናውቅም ፤ መጨረሻቸው ግን ከግብር አበሮቻቸው ጋር ትልቁ አዳራሽ (ከመናፍቃን ጎራ መሆኑን አትጠራጠሩ) ነውና ጠንቀቅ ማለት ያስፈልጋል


የጨነቀው እርጉዝ ያገባል 
ግራ የገባው አዳራሽ ይገባል…. ይሉሀል ይሄ ነው፡፡ 

የባንክ ሂሳብ ቁጥር 5026903144004 ዳሽን ፒያሳ ቅርንጫፍ መርዳት የሚፈልጉትን ብር በመላክ ልጁን ይርዱት ጉባኤውን ግን ባለመሳተፍ የሲኖዶስ ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን የሀላፊነትዎን ይወጡ፡

25 comments:

  1. የሲኖዶሱ ሥልጣንና ተግባር እስከ የት እንደሚደርስ አልገባ ብሎኛል ፡፡ የሚያወጣው መመሪያ ቤተ ክርስቲያንን ብቻ የሚመለከት መሆን አለበት ወይስ ቀበሌና መንደሩን በሙሉ ይመለከታል ፡፡ የያዛችሁት አቤቱታ መንገድ ያለው አይመስለኝም ፡፡ ቤተ ክርስቲያን የተሳሳተ ትምህርት በአውደ ምህረት እንዳይካሄድባት መከልከልና መጠበቅ ግዴታዋ ይመስለኛል ፡፡ ከዛ ያለፈው የየአዳራሹና የየሆቴሎች ስብሰባ መቆጣጠር ግን አይመለከታትም ፡፡ አንዋር መስጊድ አዳራሽ ወይም ስታድዮም ውስጥ ተፈቅዶላቸው ስብሰባ ቢያደርጉ ምን ብላችሁ ልታወሩ ነው ፡፡ ለኔ አንደኛው መፍትሄ አስቀድሞ ቤተ ክርስቲያንን ማጥራት ፣ ለህዝቡም በትምህርታቸው ያለውን መጥፎና የተሳሳተ መልዕክት አስቀድሞ ማስረዳትና ማስተማር ፡፡ ይህ ከተደረገ ማንም ዞር ብሎ አያያቸውም ፡፡ ዋናው መፍትሄና መልካሙ መንገድ ግን ሁላችሁም የአንድ እናት ልጆች ስለሆናችሁ ስምምነት የምትፈጥሩበትን መንገድ ብትመለከቱ ጥሩ ነው ፡፡ እናንተ የምትቀቧቸውን ያህል እነሱም ያቀልሟችኋል ፤ የዚህ ውጤቱ ደግሞ የምእመኑ በተወናበደ መረጃ መደነጋገርን መፍጠር ነው ፡፡ ቢቻላችሁ ቀሪውን መንገድም ፈልጉት ፡፡

    ለቤተ ክርስቲያናችን እግዚአብሔር ሰላሙን ያምጣ

    ReplyDelete
    Replies
    1. ውድ ወንድሜ ሃሳብህ ሙሉ ሙሉ የሚወድቅ ነው ባይባልም ችግር እንዳለበት ግን ሳልገልጽ አላልፍም፡፡ አሁን ከላይ የተጻፈው ጉዳይ በቤተ ክርስቲያናችን ስም መካሄድ የለበትም የሚል እንጂ በተሃድሶው ወይም በእስልምናው ስም ማካሄድ አይችሉም አይልም፡፡ አንተ የተናገርከው ሃሳብ ትክክል ሊሆን የሚችለው እነዚህ ሰዎች የሚያካሂዱትን ስብሰባ በግለሰቦች ወይም በሌላ ድርጅት ስም ቢያደርጉት ነበር፡፡ ይህንን ማድረግ ደግሞ ሕገ መንግስታዊ መብታቸው በሆነ ነበር፡፡ በቤተ ክርስቲያን ስም ግን መነገድ አይቻልም፡፡
      ብዙ ምዕመናን ግራ የሚጋቡት በትክክለኛ (የቤተ ክርስቲያን) ልጆች በሚያዘጋጁት ጽሁፍ ሳይሆን ግራ የገባው አስተያየት በሚሰጡ ሰዎች ሃሳብ ነው፡፡
      የአንዳድርገን ብሎግ ማናጀሮችንም ማለት የምፈልገው የተሰጠው አስተያየት ሁሉ ፖስት መደረግ የለበትም የሚል ነው፡፡ ነጻ ሃሳብ እናስተናግዳለን ማለት ሕዝበን የሚያውክ ሃብ ያላቸውን ሃሳብ እናስተናግዳለን ማለት ነው የሚል አቋም የለኝም፡፡ ስለዚህ እየተመረጡ ፖስት ቢደረጉ መልካም ነው፡፡ ጽሁፎቻችን በማስረጃ የተደገፉ እስከሆኑና ወቅቱን ጠብቀው (ወቅቱን ጠብቆ ማለት ፍጥነትን አይወክልም) ውጤት በሚያስመዘግቡበት ሰዓት ፖስት ከተደረጉ በሰውም በእግዚአብሔርም ዘንድ ሞገስን ያሰጣችኋል፡፡

      እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡

      Delete
    2. ውድ ወንድሜ ሃሳብህ ሙሉ ሙሉ የሚወድቅ ነው ባይባልም ችግር እንዳለበት ግን ሳልገልጽ አላልፍም፡፡ አሁን ከላይ የተጻፈው ጉዳይ በቤተ ክርስቲያናችን ስም መካሄድ የለበትም የሚል እንጂ በተሃድሶው ወይም በእስልምናው ስም ማካሄድ አይችሉም አይልም፡፡ አንተ የተናገርከው ሃሳብ ትክክል ሊሆን የሚችለው እነዚህ ሰዎች የሚያካሂዱትን ስብሰባ በግለሰቦች ወይም በሌላ ድርጅት ስም ቢያደርጉት ነበር፡፡ ይህንን ማድረግ ደግሞ ሕገ መንግስታዊ መብታቸው በሆነ ነበር፡፡ በቤተ ክርስቲያን ስም ግን መነገድ አይቻልም፡፡
      ብዙ ምዕመናን ግራ የሚጋቡት በትክክለኛ (የቤተ ክርስቲያን) ልጆች በሚያዘጋጁት ጽሁፍ ሳይሆን ግራ የገባው አስተያየት በሚሰጡ ሰዎች ሃሳብ ነው፡፡
      የአንዳድርገን ብሎግ ማናጀሮችንም ማለት የምፈልገው የተሰጠው አስተያየት ሁሉ ፖስት መደረግ የለበትም የሚል ነው፡፡ ነጻ ሃሳብ እናስተናግዳለን ማለት ሕዝበን የሚያውክ ሃብ ያላቸውን ሃሳብ እናስተናግዳለን ማለት ነው የሚል አቋም የለኝም፡፡ ስለዚህ እየተመረጡ ፖስት ቢደረጉ መልካም ነው፡፡ ጽሁፎቻችን በማስረጃ የተደገፉ እስከሆኑና ወቅቱን ጠብቀው (ወቅቱን ጠብቆ ማለት ፍጥነትን አይወክልም) ውጤት በሚያስመዘግቡበት ሰዓት ፖስት ከተደረጉ በሰውም በእግዚአብሔርም ዘንድ ሞገስን ያሰጣችኋል፡፡

      እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡

      Delete
    3. Here is yetewahido lijjjjj. These folks are politicians not orthodox christian. They will never be ready for reconcilation.

      Delete
    4. አንተ ሰው ነቢይ ሆነሃል መሰለኝ ፡፡ ከተጻፈው ውስጥ በቤተ ክርስቲያን ስም የሚል ጽሁፍ እኔ አላነበብኩም ፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ የማታውቀውና ከቤተ ሥርዓት ውጭ የሚሉ ቃላት ተደጋግመው ተገልጸዋል እንጅ ፣ የትም ቦታ ላይ በኢተዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስም እርዳታ ሊጠይቁ ነው አይልም ፡፡ ስለዚህም ሳንሱር ማድረግ የተለመደ ቢሆን ያልተጻፈውን እያነበቡ በስሜት የሚነዱትን ሰዎች ጽሁፍ መግታት ያስፈልግ ነበር ፡፡ ጥያቄአችሁ አልገባኝም ፤ የሲኖዶሱ ስልጣን እስከምን ይሄዳል ? ማግኘት የምትችሉ ከሆነ የሰላምን መንገድም ፈልጉ ማለት ምኑ ከፋብህ ፡፡ ነገሩን በዝርዝር የምታውቅ ከሆነ ፣ የምታውቀውን ምስጢር ለማናውቀው ግለሰቦች ብታስረዳ የተሻለ አካሄድ ይሆን ነበር ፡፡ እኔ ሲኖዶስ መንግሥት የሆነ ያህል ፣ በየቦታውና በየስርቻው የሚደረገውን ስብሰባ ሁሉ ያግድ ሲባል ፣ ለአእምሮዬ ትክክል ስላልሆነልኝ አስተያየቴን አቅርቤአለሁ ፡፡ አሁንም ለዚህ ጥያቄ ማብራሪያ ካለህ ወዲህ በለው ፡፡ በወገንህ ክፍል ላይ የጭፍን ጥላቻ አታድርግ ፤ እንደ ክርስቲያን የሚስማሙበትን ማሰብ ነው እንጅ ፣ ነገሮችን ለማባባስ ከዳር ሆነን እንደ ዲያብሎስ አናራግብ እላለሁ ፡፡ ካቃተን ካቃተ እንደ ሌሎቹ ቤተ እምነቶች ከቤተ ክርስቲያን ተለይተው ለራሳቸው ህዝብ የሚያስተምሩበትንና የቤተ ክርስቲያናችን ሰላም የሚፈጠርበትን ምክር መሰጠት አለብን እንጂ ፣ ሰውነታቸውን በመካድ ፣ በየትም ቦታ አትታዩ ማለት አያስኬድም ፡፡ ማንኛውም ዜጋ የተሰጠው ህጋዊ መብት አላቸውና ባንፈቅደውም ይንቀሳቀሳሉ ፡፡ አስተሳሰባችንን ሰፋ አድርገን ነገሮችን እንመልከት ፡፡

      እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ

      Delete
    5. እኔ ያነበብኩት
      1. ከቤተ ክርስቲያኗ ፍቃድ ውጭ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን አማኞችን በመጥራት ምናፍቅናቻን በማር ላይ ለማቅረብ ዝግጅት እንዳደረጉ የሚል አለ
      2. ሰውን ከቤተ ክርስቲያን ሲያርቁ የተመለከቱት አባቶቻችን ከስርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጭ ነው ማለታቸውን
      3. የኛ ያልሆኑ አስተማሪዎች እኛን ወክለው በየትኛውም መድረክ ላይ ማስተማር አይችሉም ፤ በተለያየ ቦታ የሚደረጉ ጉባኤዎች ከስርዓተ ቤተ ክርስያን ውጪ ናቸው
      4. ቤተክርስያንን የማይወክሉ ሰዎች ጋር ተጠግጦ ስርዓተ ቤተክርስትያን እየተጣሰ የሚደረገውን ህገ ወጥ ተግባር እንቃወማለው ፤ ስርዓት ከተጠበቀ ሁሉን በስርዓት ማድረግ ይቻላል
      5. የተሐዲሶ መናፍቃን አቀንቃኞች ምን ያህል ቤተክርስቲያንን ለመበረዝ አጋጣሚዎችንና ቀዳዳዎችን እየፈለጉ
      6. ቤተክህነቱ ከቤተክርስትያን ውጪ የሚደረጉ ጉባኤዎችን ከቻለ በራሱ ካልቻለ ከፖሊስ ጋር በመሆን ቤተክርስትያኒቷ የማታውቃቸው መሆኑን አስገንዝቦ ማስከልከል መቻል አለበት ፤ የቤተክርስትያኒቷ ስም የሚደረጉ ህገወጥ ጉባኤዎች እንዳይደረጉ ማስቻልም አለበት

      ወንድሜን ነቢይ አድርጌ ወቅሼህ ነበር ፡፡ በተራ ቁጥር ስድስት የተጠቀሰውን የቤተ ክርስትያኒቷ ስም የሚለውን በቤተ ክርስቲያን ስም ብዬ ስላልተረዳሁት ነውና ይቅርታ ፣ በቀረበው ጽሁፍ ላይ እኔ እንደማደርገው ግድፈት እንዳለ ይታያል ፡፡ ወቀሳውን አብረን እንካፈል ፡፡ እኔ የጐደለውን ቃል አስተካክዬ የተረዳሁት የቤተ ክርስቲያኒቷ ስም እንዳይጠፋ ህገወጥ ጉባኤዎች እንዳይደረጉ ማስቻል አለበት በማለት ነበር ፡፡ ያየኸውን አሁን በማስተካከል ለማየት ችያለሁ ፡፡

      Delete
    6. betekiristiyanua akmua kefekede aydelem bekebele dereja gudguad wistm bihon besimua yemikahedu minfiknawochin mekawem bilom maskom mebtua new. silelelaw aymeleketenm.

      Delete
  2. Very good AndiAdrigen. This is the wise way to fight Tehadisos.

    ReplyDelete
    Replies
    1. ምን አገባህና የቤትህ ጓዳ አደረከው እንዴ ዜጎች እኮ በእኩልነት የሚኖሩባት ሐገር እኮናት ማንን ትምክህተኛ፣ ወሬኛ ፣ጉልበተኛ የሚፈነጭባት ሀገር አይደለችም በስንቱ ደምና አጥንት የተጠበቀች ናት የተጎዳ ይረዳ ሲባል ያዙኝ ልቀቁኝ ውርደት ነው ለወገን መጨከን፡፡

      Delete
    2. Poletika Mehonwa new? /kkkkk/ . eski e'nsak በስንቱ ደምና አጥንት የተጠበቀች ናት kkkkkk/Jemari poletikena mehonihin anten manager alasfelegenim/

      Delete
  3. ማን ነው ፈራጅ ያደረጋችሁ? ወይ አትረዱ ወይ ደግሞ እንዲረዳ አታደርጉ፣ አቤት ሰይጣንነት እግዚአብሔር ይገስጻችሁ!! ሰይጣኖች፡፡ ከለባት ራሳችሁ ናችሁ እሺ?

    ReplyDelete
  4. you are right! let us fight tehadiso and pass this message to anyone around us! May God protect our church

    ReplyDelete
    Replies
    1. keman gar new yemetetalaw?megadelachen kedemena kesega gar ayedelem

      Delete
  5. Egzeabher yabertachu lela min yibalale

    ReplyDelete
  6. Good comment the following anonymous I suppoort ur idea
    We have to fight TEHADESO (Modern protestanism. )who using our pure tewahedo name , Good jon Andadrgen keep up the Godd job guys.

    ውድ ወንድሜ ሃሳብህ ሙሉ ሙሉ የሚወድቅ ነው ባይባልም ችግር እንዳለበት ግን ሳልገልጽ አላልፍም፡፡ አሁን ከላይ የተጻፈው ጉዳይ በቤተ ክርስቲያናችን ስም መካሄድ የለበትም የሚል እንጂ በተሃድሶው ወይም በእስልምናው ስም ማካሄድ አይችሉም አይልም፡፡ አንተ የተናገርከው ሃሳብ ትክክል ሊሆን የሚችለው እነዚህ ሰዎች የሚያካሂዱትን ስብሰባ በግለሰቦች ወይም በሌላ ድርጅት ስም ቢያደርጉት ነበር፡፡ ይህንን ማድረግ ደግሞ ሕገ መንግስታዊ መብታቸው በሆነ ነበር፡፡ በቤተ ክርስቲያን ስም ግን መነገድ አይቻልም፡፡
    ብዙ ምዕመናን ግራ የሚጋቡት በትክክለኛ (የቤተ ክርስቲያን) ልጆች በሚያዘጋጁት ጽሁፍ ሳይሆን ግራ የገባው አስተያየት በሚሰጡ ሰዎች ሃሳብ ነው፡፡
    የአንዳድርገን ብሎግ ማናጀሮችንም ማለት የምፈልገው የተሰጠው አስተያየት ሁሉ ፖስት መደረግ የለበትም የሚል ነው፡፡ ነጻ ሃሳብ እናስተናግዳለን ማለት ሕዝበን የሚያውክ ሃብ ያላቸውን ሃሳብ እናስተናግዳለን ማለት ነው የሚል አቋም የለኝም፡፡ ስለዚህ እየተመረጡ ፖስት ቢደረጉ መልካም ነው፡፡ ጽሁፎቻችን በማስረጃ የተደገፉ እስከሆኑና ወቅቱን ጠብቀው (ወቅቱን ጠብቆ ማለት ፍጥነትን አይወክልም) ውጤት በሚያስመዘግቡበት ሰዓት ፖስት ከተደረጉ በሰውም በእግዚአብሔርም ዘንድ ሞገስን ያሰጣችኋል፡፡

    እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡

    ReplyDelete
  7. it is good but tehadso please come to church and the church is ready if u come to niseha. let mariam help u. now it is fasting please soon come to church through niseha.

    ReplyDelete
  8. Ohhhhhhh!!!! please God for give us !!!!!!

    ReplyDelete
    Replies
    1. ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ሁሌም ከኛ ጋር ነው፡፡ የለመነውንም ሁሉ ይፈፅምልናል፡፡

      Delete
  9. ማነው እናንተን ለሀማኖት ታፔላ ለጠፊ ያረጋችሁ ስማ አመንገድ ወድቆ ለኔቢጤ ሳንቲም መስጠት ብቻ መስሎ ከታየህ ጽድቅ ተሳስተሐላል አጂህ ላይ ወድቆ የረጂያለህ የሚል ወንድምን መሰናክል መሆንና ለሞት ማድረስ ከየት የመጣ መሰለህ የዚች ሐገር ዜጋ ነው እኮ የሌላ እምነት ተከታ መሆን እኮ ሞት አያስፈርድም ምንአይነት አይን ያወጣ ጭካኔ እንደሆነ አይጋባኝኝም የቅናት መንፈስ እንዲህ ለካ አእምሮን ያሸጣል ለሐየማኖት እንኳን ብትቀኑ ጥሩ እናንተ ግን ተበለጥን ብላችሁ ነው እኮ ቁጭ ብላችሁ ነው እኮ የተቀደማችሁት ገናምን አይታቸሁ እውነት ትዘገያለች እንጂ አትጠፋም ህገምንግስታዊ ምናምን ሁሉም የመኖር መብትና የህችን ሐይማኖት የመከተል መብት አለው የማህበሩ አባል ካልሆነ አሁኑኑ ተፈርዶበታል ነው የእናንተ አባባል አባል አንሆንም ኦርቶዶክስ እምነትን እንከተላለን የፈለግነውን የቤተክርስቲያኗን ሰባኪና ዘማሪ እናዳምታለን ምን ትሆን የዘመኑ መጨረሻ ላይ ነን ያለነው እርስ በርስ ክፍፍል ጠብ ክርክር ይበዛል የህደግሞነው ሊመጣ ግድ ነው ታወራለህ እንጂ ማረጋገጫ የለህም የተዋዋሉትን የተፈራረሙትን አምጣ በለው ቆርጦ ቀጥል ብሲዲ አትመን ይህ ነው እውነተኛነት ገበያ አጣሁ ብሎ ህዘበ ክርስቲያኑን ማመስ በወሬና በቲፎዞ መመካት በሰማይም በምድርም ያስቀጣል እግዚብሄር እውነቱን ይግለጥልን
    ድንግል ከነልጂዋ ትጠብቀን !!!!!

    ReplyDelete
  10. የባንክ ሂሳብ ቁጥር 5026903144004 ዳሽን ፒያሳ ቅርንጫፍ መርዳት የሚፈልጉትን ብር በመላክ ልጁን ይርዱት ጉባኤውን ግን ባለመሳተፍ የሲኖዶስ ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን የሀላፊነትዎን ይወጡ፡

    ReplyDelete
  11. yehe besawe laye mefreda sayhon atesasatu..... "birhan kechelama mene hibret alewe " yemlew kale mefetsem nawe .... enezehe memeher nane bayoche besinodose sebesaba cheger selalbachaw gudayachew tayto legenbotu melat gubaye yedresa tablulaena betegesete metebake senorbachew bemanalebegnenate medreka lamazegajet memokaer korthodox lij sayhon kedyablose yemetebek sera nawe :: selezehe yazagajuten yedarashe sebesaba enkawomalen ::

    ReplyDelete
  12. inante azagn yemeselachihihu wushoch,demo bilachihu bilachihu adarashun hulu mekotater felegachihu?? yefelagachew bota lay hedew programachewin makahed mebtachew new. inante saytan yeketerachihu yeseytan kitiregnoch nachihu yegeta wongel indaysebek yemitificherecheru yeseytan mesaria.benante yetenesa sint sew new kebetekirsitian yewetaw.

    o igzine iyesus christos ikiba lebetekristianike kidist

    ReplyDelete
    Replies
    1. yesidibin kal yemitiageru hulu enenite rasachihu yetehadisoawiyan chirawoch nachihu yohanis beraiyou endalew "bemechershaw zemen kidusanin lisadeb maderiwin lisadeb yesideb afun kefete" endalew benanite tefetseme "anonymous" negn kemitelu "ARYOS" negn betilu yashalachihual

      Delete
  13. o igizien iyesus christos ikeba lebetekiristianike kidist imafe mahberekidusan(im afe kelb or mahberekidusan gebru lediabilos)

    ReplyDelete