Wednesday, February 1, 2012

ቤተክህነቱ አዳራሹን ለተሀድሶ አቀንቃኞች ሳይፈቅድ ቀረ


(አንድ አድርገን ጥር 23  2004 ዓ.ም)፡- ጥር 20 /2004 ዓ.ም የተሀድሶያውያን ስብስብ ሊያደርጉት የነበረው  ጉባኤ ከለባት የቤተክህነቱ  ጥያቄ መመለስ ስላልቻሉ  ጉባኤው ሳይደረግ እንደዋለ ለማወቅ ችለናል ፤ የቤተክህነቱ ሀላፊዎች ቀደም ብለው አዳራሹን ለጉባኤ የፈቀዱ መሆኑ ቢታወቅም በመጨረሻ ጉባኤውን ሊያደርጉ ያሰቡትን ሰዎች ‹‹ እዚህ ቤተክህነት አዳራሻ ላይ ቤተክርስትያንን የሚወክሉ መምህራን ከሆነ እንደሚፈቅዱ ያለበለዚያ ግን በስመ እርዳታ ቤተክርስትያንን የማይወክሉ በሲኖዶስ ጉባኤ  የታገዱ ሰዎች ከሆኑ እንደማይፈቅዱላቸው›› እርግጡን ነግረዋቸው ጉባኤው ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡ ከጉባኤው ሁለት ቀናት በፊት ጉባኤው እንደተሰረዘ  በቤተክህነት ሰሌዳ ላይ ቤተክህነቱ ማስታወቂያ ለጥፏል፡፡ በዚህ ጉባኤ አለመካሄድ ጥቂት ሰዎች ከእነርሱ ወገን የሆኑ ሰዎች መካሄድ አለበት ብለው ብዙ ቢሮዎች ቢያንኳኩም በበሬ ወለደ ድህረ ገፃቸው አማካኝነት ቢፅፉን በሩን የሚከፍት ሰው ሊያገኙ አልቻሉም፡፡

 እኛ ጉባኤውን የተቃወምንበት ምክንያት ስርዓተ ቤተክርስትያን ይከበር ፤ የሲኖዶስ ውሳኔዎች ተግባራዊ ይሁኑ ፤ ከሚል አቋም እንጂ ከሌላ አለመሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያስተላልፋቸው ውሳኔውች በቤተክርስትያኗ የተለያየ የስልጣን ደረጃ የሚገኙ አገልጋዮች ጀምሮ እስከ ጳጳሳት ድረስ የሚገኙ ኃላፊዎች የማስፈፀም ግዴታ አለባቸው ፡፡ እኛም ስርዓት ሲጣስ እያየን ዝም አንልም ፤ የሲኖዶስ ውሳኔዎች ለተግባራዊነታቸው የሚያጋጥማቸውን እክሎች ያየነውን እናንተው ጋር እናደርሳለን፡፡


አቶ በጋሻው ደሳለኝ እና መሰሎቹ እንቅስቃሴያቸውን ወደ  አሜሪካ   በማድረግ ላይ ይገኛሉ ፤ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ተንቀሳቅሰው እንዳይሰብኩ ፤ አውደ ምህረት ላይ እንዳይቆሙ ከሲኖዶስ ከተወሰነ በኋላ መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው እይታቸውን ከኢትዮጵያ ውጪ ወደ አሜሪካ ላይ አድርገዋል ፤ ዘርፌ ከበደ ከወራት በፊት አሜሪካ በመሄድ ፤ ትዝታው ሳሙኤልን ማስከተል ችላለች ፤ ቀጥሎም ባለን መረጃ መሰረት መሰሎቻቸው ተከትለው በብቸኛው አየር መንገዳችን ፤ እዚህ ያልተሳካውን እዛ ለመጀመር ጉዞ ያደርጋሉ ብለን እንገምታለን ፤ ጥር 2004 ላይ አቡነ ፋኑኤል ወደ ዲሲ ሲኖዶስ ሲልካቸው ሳሪስ አካባቢ በሚገኝው ቤታቸው እስከ ለሊቱ ስድስት ሰዓት ድረስ ስለ አሜሪካ ጉዞ ሲወያዩ አምሽተዋል ፤ በጊዜው በጋሻው ደሳለኝን በአሜሪካ የስብከተ ወንጌል ሀላፊ አድርገው ለመሾም ቃል የገቡለት ቢሆን አቶ በጋሻው ከአሜሪካ ኢምባሲ በር የማያደርስ ስራ ከ2ዓመት በፊት ስለሰራ ደፍሮ ኢምባሲ ለመሄድ ልቡ አልከጀለም ፤ ከአቡነ ፋኑኤልም ጋር አብሮ ሊሄድ አልቻለም ፤ ወደፊትም አይሄድም ( በኢምባሲው ያቀረበውን የስህተት ማረጃ ጉዳይ ካላነሳለት) ፤ ባለፈው ሳምንት በቤተክህነት አዳራሽ ሊያደርጉት የነበረው ጉባኤ ተሰርዟል፤ ይህ ተሰረዘ እና ሰዎቹ ይተኛሉ ማለት አይደለም ፤ እኛም ከተኛንበት ነቅተናል ፤ የእንቅልፍ ዘመናችንም አልፏል ፤ ቤተክርስያንን ስርዓት እንዳይጣስ ከመሰል ሰዎች ለመጠበቅ በሄዱበት እየሄድን ባደሩበት እያደርን ፤ በተሰበሰቡበት እየተሰበሰብን መረጃዎችን እናንተው ዘንድ እናደርሳለን ፤ ጊዜው የመረጃ ዘመን ነው ፡፡ ያገኝነውን መረጃ እውነታ እስካለው ድረስ ለማንም ብለን አንደብቅም፡፡  ፤
አሁንም ደግመን መናገር የምንፈልገው ነገር የልብ ህመም የደረሰበት ወንድማችን የሚያስፈልገውን ገንዘብ ያህል ለማሰባሰብ ይረዳው ዘንድ ቤተክርስትያኗ ፍቃድ ከሰጠቻቸው መምህራን ጋር ጉባኤ ቢያዘጋጁ መልካም ነው እንላለን፡፡ እኛም ብዙ ሰዎች በጉባኤው እለት እዲገኙ የቻሉትን ያህል እንዲረዱ የአቅማችንን ያህል በመስራት ከጎኑ ለመቆም ቃል እንገባለን፡፡

ሌላ ዜና
  • በባቦጋያ መድሐኒአለም ቤ/ን ካህናትና የተለያዩ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር አካላት ከዚህ በፊት የቤተክርስትያንን መሬት ያለአግባብ የሸነሸኑት ሳያንሳቸው ፤ በህዝቡ አማካኝነት ከታሸጉት ቢሮዎች ውስጥ የተለያዩ ሰነዶችን ፤ ማህተብን አውጥተው ሲሄዱ በህግ አካላትና በምእመኑ ትብብር ተይዘዋል፡፡  ‹‹አሁንስ ሰው  ናፈቀን›› የሚያስብል ጊዜ ላይ የደረስን ይመስለናል
  • በደቡብ ክልል ጋሞጎፋ ዞን ጨንጫ ከተማ የእመቤታችን በዓል ቀን ጥር 21 /2004 ዓ.ም  አንድ ፕሮቴስታን የሆነ ፖሊስ በዓሉ በሚከበርበት ወቅት ተኩስ በመተኮስ አንድ ወጣት ያቆሰለ ሲሆን ፤ የተጎዳው ወጣት ወደ ሀኪምቤት ሲሄዴ የተኮሰው ፖሊስ ባደረሰው አደጋ  ወደ እስር ቤት ወርዷል፡፡(ጉዳዩን አጣርተን ሌላጊዜ እንመለስበታለን)



13 comments:

  1. Lebego new ketikit gizeat behuala bin bilew yitefalu

    ReplyDelete
  2. thanks for the timely update!

    ReplyDelete
  3. Good job for those who are following instruction/direction from Synodos.

    Right now it is up to us -YETEWAHIDO LIJOCH- to protect our church. We need to get up and take responsiblity to protect our church and maintain our belief. We need to wake up and pay attention to what is going on arround our church. If there is some thing positive support it, if there is some thing negative go against it openly, quickly, and effectively!!

    God Bless Orthodox Tewahido

    ReplyDelete
  4. Ajans France blogs hoye!!!!!!!!!!!!

    አቤቱ የምታደርጉትን አታውቁምና ይቅር ይበላችሁ። ምን አይነት የተረገማችሁ ጠማማ ትውልድ ናችሁ እውነት እውነት እላችሁአለሁ ሰማይና ምድር ያልፋሉ ፤ የእግዚአብሔር ቃል አያልፍም። እናንተ የዘመኑ የእየሱስ ክርስቶስ ሰቃዮች፣ ለምን የክርስቶስ ወንጌል ተሰበከ ብላችሁ በቅናት እውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆችን ማሳደድ እንደ ፈሪሳዊያን ለቤተመቅደሳቸው የቆሙ መስሉአቸው ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስን እስከ ሞት ያደረሳችሁ የዘመኑ ፈሪሳዊያን ሆይ፣ የምትቀልዱትና የምትጫወቱት ከእሳት ጋር ነው።

    ምንም አላችሁ ምንም የሚሰማችሁ የለም። እግዚአብሔርን የያዘ ሁልጊዜም አሸናፊ ነው። አሁን ማ ይሙት ይህንን ዝግጅት እናንተ \ማ፡ሰ\ ስላላዘጋጃችሁ ቅናት አቃጠላችሁ እንጂ በእውነት የታገደ፣ የተከለከለ በመሆኑ አይደለም። የእግዚአብሔርን ቃል ለመመስከርና በጎ ሥራ ለመስራት ማንም አያግድም፣ ማንም አይከለክልም። ቢከለከል ኖሮ የሚከለከለው እናንተን ለመሰሉ የሐሰት ክርስቲያን ነበር። ዳሩ ግን እኮ መምህራችን እየሱስ ክርስቶስ ፤ በኔ ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ነገር ግን አሸናፊዎች ናችሁ ብሎ ስለአስተማረን በዚህ እስከመጨረሻው ድረስ እንፀናለን። ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የምታገለግሉት ጌታ ከእናንተ ጋር ስለሆነ አይዙአችሁ። ጊዮርጊስ
    ፅና ፅና ፅና። ጠላት ግን ከነሠራዊቱ ወደ ጨለማ ይውረድ። ልብ ይስጣችሁ።
    አይ የኤደኑ ገነት እባብ ማቅ ኪኪኪኪኪኪኪኪ--------------------

    ReplyDelete
    Replies
    1. እኔ የሚገርመኝ ሁል ጊዜ አንድ ያቀዳችሁት አፍራሽ ስራ በእግዚአብሔር ኃይል ሲፈርስ የምታመካኙት በማህበረ ቅዱሳን ላይ ነው ፡፡ ለኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪዋ ማህበረ ቅዱሳን ብቻ ነው ያለው ማን ነው? ይህ የሁሉም አማናዊ ኦርቶዶክስ ግዴታ ስለሆነ አትሳሳቱ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ስለ ክርስቶስ ጥንትም ስትሰብክ ነበር ዛሬም ትሰብካለች ወደፊትም እስከ ምጽአት ድረስ ትሰብካለች፡፡ ነገር ግን የምትሰብው እንደ እናንተ የመናፍቃንን ዶግማ ቋንቋና የስብከት ዘዴ ተጠቅማ ሳይሆን ከሐዋርያት የተረከበችውን በሊቃውንት የተተረጎመላትን እውነተኛውን ኢየሱስ ክርስቶስን ትሰብካለች፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ካላደስን ብላችሁ ይህን ያህል አትገበዙ፡፡ የይቅርታና የምህረት አምላክ ንቦናችሁን ወደ አማናዊቷ ቤተ ክርስቲያን ይመልስላችሁ፤፤

      Delete
    2. Dedeb!!! Simu yikebidihal!!

      Delete
    3. "ይህ ተሰረዘ እና ሰዎቹ ይተኛሉ ማለት አይደለም ፤ እኛም ከተኛንበት ነቅተናል ፤ የእንቅልፍ ዘመናችንም አልፏል ፤ ቤተክርስያንን ስርዓት እንዳይጣስ ከመሰል ሰዎች ለመጠበቅ በሄዱበት እየሄድን ባደሩበት እያደርን ፤ በተሰበሰቡበት እየተሰበሰብን መረጃዎችን እናንተው ዘንድ እናደርሳለን ፤ ጊዜው የመረጃ ዘመን ነው ፡፡ ያገኝነውን መረጃ እውነታ እስካለው ድረስ ለማንም ብለን አንደብቅም"
      አዎ አንተኛም የገሃነም ደጆችም አይችሏትም እንደተባለው አትችሏትምና እባካችሁ ስራ ቀይሩ:: በጣም ያልገባኝ ግን ምኞታችሁ ሁሉ ቢሳካ መጨረሻ ላይ ምን መሆን እንደምትፈልጉ ነው::

      Delete
  5. Ajance France hoye!!!!!!!!!!!!!!!

    አቤቱ የምታደርጉትን አታውቁምና ይቅር ይበላችሁ። ምን አይነት የተረገማችሁ ጠማማ ትውልድ ናችሁ እውነት እውነት እላችሁአለሁ ሰማይና ምድር ያልፋሉ ፤ የእግዚአብሔር ቃል አያልፍም። እናንተ የዘመኑ የእየሱስ ክርስቶስ ሰቃዮች፣ ለምን የክርስቶስ ወንጌል ተሰበከ ብላችሁ በቅናት እውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆችን ማሳደድ እንደ ፈሪሳዊያን ለቤተመቅደሳቸው የቆሙ መስሉአቸው ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስን እስከ ሞት ያደረሳችሁ የዘመኑ ፈሪሳዊያን ሆይ፣ የምትቀልዱትና የምትጫወቱት ከእሳት ጋር ነው።

    ምንም አላችሁ ምንም የሚሰማችሁ የለም። እግዚአብሔርን የያዘ ሁልጊዜም አሸናፊ ነው። አሁን ማ ይሙት ይህንን ዝግጅት እናንተ \ማ፡ሰ\ ስላላዘጋጃችሁ ቅናት አቃጠላችሁ እንጂ በእውነት የታገደ፣ የተከለከለ በመሆኑ አይደለም። የእግዚአብሔርን ቃል ለመመስከርና በጎ ሥራ ለመስራት ማንም አያግድም፣ ማንም አይከለክልም። ቢከለከል ኖሮ የሚከለከለው እናንተን ለመሰሉ የሐሰት ክርስቲያን ነበር። ዳሩ ግን እኮ መምህራችን እየሱስ ክርስቶስ ፤ በኔ ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ነገር ግን አሸናፊዎች ናችሁ ብሎ ስለአስተማረን በዚህ እስከመጨረሻው ድረስ እንፀናለን። ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የምታገለግሉት ጌታ ከእናንተ ጋር ስለሆነ አይዙአችሁ። ጊዮርጊስ
    ፅና ፅና ፅና። ጠላት ግን ከነሠራዊቱ ወደ ጨለማ ይውረድ። ልብ ይስጣችሁ።
    አይ የኤደኑ ገነት እባብ ማቅ ኪኪኪኪኪኪኪኪ--------------------

    ReplyDelete
  6. Calling Them Tehadiso is Wrong
    The secret mission of heretics should not be called ‘tehadiso’ because, in my view, the use of the word 'tehadiso' to explain something wrong, negative, heresy, is basically misusage of the word. Under no circumstance the good word 'tehadiso' can be used to mean heresy/heretic. It always has a positive meaning. If one says 'tehadiso menafikan' it means 'menafikan' who abandoned heresy and become True Christians, not who changed to 'minfikina.' What those 'menafikan' say is negative about our church: cut this, shorten that, this is long, that is unnecessary, do not praise or prostrate for Virgin Mary, the Angels, and Saints... Etc. They are trying to change the good traditions, canon and dogma of the church that lead to eternal life to something earthly and ugly. This is heresy, not 'metades'. We, Christians, need 'metades'. There is not another context to use the word 'tehadiso' to mean 'nufake'. Things are reformed to be better, not to become worse. Those who started to use this nice word to describe something wrong need to use appropriate words or phrases because we need to use the word ‘TEHADISO’ in our church and in Christians lives. Hence, as our church calls them 'menafikan', we just have to call them 'menafican or ‘wushoch’ or atsirare betekirstian. Also, in my opinion, the expression that says, ‘BETEKIRSTIAN ATITADESIM IS WRONG.’ I argue that BETEKIRSTIAN NEEDS TEHADISO! The question should be what kind of tehadiso? I would say BETEKIRSTIAN as an association of Christians needs TEHADISO when its members practice unchristian values, when disagreements and disunity exist among them, when they fail to carry their mission of preaching the redemption paid by Lord to mankind to those who are afar from this eternal life, and so on. In addition, when an individual Christian leads unchristian life and engulfed in a sea of sin, he/she needs TEHADISO. Besides, when the church’s overall leadership and bureaucratic management is in disarray, it needs TEHADISO! Thus, I believe that now is the time for all of the above to undertake TEHADISO!
    Egizeabihare hulachininm lemetades yabikan. Amen!

    ReplyDelete
    Replies
    1. ሃይማኖት የምንቀበለውና የምንጠብቀው እንጂየምንሠራውና የምናሻሽለው አይደለም………..ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ልዩ የሚያደርጋት ብቻ ሳይሆን ከትክክለኛነቷ ማረጋገጫዎች አሁንም ዋነኛዋ መገለጡ ነው፡፡ የሌሎቹ በተለይም ከኢንዱስትሪው አብዮት በኋላ የተነሡ የክርስትና ክፍልፋዮች /Denominations/ ሁሉ መሠረተ እምነታቸው የሚዋቀረው በዩኒቨርስቲዎችና በየተቋማቱ ባሉ ምሁራኖቻቸው አስተምህሮ በጠረጴዛ ዙሪያ ነው፡፡ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የሚመሠረተው ግን በገዳማውያን ቅዱሳን መገለጥ ላይ ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ እስካሁን ሊቃውንቱ ሁሉ በመማር ብቻ ሳይሆን በገዳም ተወስነው፣ ሱባኤ ገብተው፣ በእርሱ መገለጥ የተሰወረ ምስጢር ይገለጥላቸዋል፤ የረቀቀው ይጎላላቸዋል፡፡ ያንን ብቻ ያስተምራሉ፤ እርሱንም ብቻ ይዘን እናስተምራለን፤ በተገለጠውም መሠረት እንኖራለን፡፡ በእኛ ሀገር እንኳን እነ ቅዱስ ያሬድ፤ አባ ጊዮርጊስ፣ አባ ዜና ማርቆስ፤ አባ ተክለሃይማኖት፣. . . ሁሉም በሱባኤ፣ በገዳም፣ በምናኔ፣ በተጋድሎ ተወስነው፤ በተገለጠውና በሚገልጥላቸው መንገድ ብቻ ተጓዙ፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትም የሚያረጋግጡልን ይህንኑ ብቻ ነው፡፡ ሃይማኖትን እንቀበለዋለን ከዚያም እንጠብቀዋለን እንጂ ልንሠራው አንችልም፡፡ የያዕቆብ ወንድም ቅዱስ ይሁዳ «ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችኋለሁ» /ይሁ.1፥3/ ሲል እንደገለጸልን፤ ሃይማኖት ለቅዱሳን በመገለጥ የተሰጠች እንጂ የተሠራች አይደለችም፡፡ ጌታችንም በወንጌል «ከዓለም ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገለጥሁላቸው፡፡ የአንተ ነበሩ ለእኔም ሰጠሃቸው፤ ቃልህንም ጠብቀዋል፡፡ የሰጠኸኝን ሁሉ ከአንተ እንደሆነ ያውቃሉ፤ የሰጠኸኝ ቃል ሰጥቻቸዋለሁና፤ እነርሱም ተቀበሉት. . .» /ዮሐ.17፥22/ ሲል እንዳስተማረው፤ ክርስትና የተቀበልነውና የምንጠብቀው እንጂ የሠራነውና የምናሻሽለው አይደለም፡፡…. ከዲያቆን ብርሃኑ አድማስ ትምህርት የተወሰደ https://www.facebook.com/notes/birhanu-admass-anleye

      Delete
    2. ከላይ ደደብ ብለህ የተሳደብከዉ ወንድሜ ደደብ ብለህ መሳደብህ ራሱ ያንተን ማንነት ይገልጻል :: ማፈሪያ

      Delete
  7. 'Eyerusalem hoy biresashkegne tirsagn'ewnetegna yetewahido lijoch ayzoachu bertuln beteley merejawchn beyeletu lemiemenan bemadres 'yeseytan' alama endaysaka.Enegnh 'tehadso menafikann'and wokt KIRSTOS bejrafu gerfo yaswetachewalna.Bewnet ersu libonachewn ymels amen.

    ReplyDelete
  8. ለመሆኑ ማህበረ ቅዱሳን በምን ጥፋቱ ነው የሚወቀሰው አድባራትን ገዳማትን ስለአገለገለ የተዋህዶን ትምህርት ስላስተማረ መወቀስስ የሚገባው ሳይማር አማርኛን ብቻ አጣፍጦ በመናገር ቤተክርስቲያንን ለመሸጥ የተዘጋጀው ወገን ነው ለነገሩ በተዋህዶ ላይ ታቅዶ የነበረው ሴራ በአባቶች በወንድሞችና በእህቶች አማካኝነት ስለከሸፈ ምናልባት ወደ ውጪው ዓለም ሄደው እዛም እስኪታወቁ ድረስ ጥቂት ሊያታልሉ ይችላሉ የዚህ ድረ ገጽ አዘጋጆችም መረጃ ማቅረባችሁን ቀጥሉበት
    እግዚአብሔር ተዋህዶን ይጠብቅልን አጽራረ ቤተክርስቲያንን ያስታግስልን አሜን
    ሰሎሞን በ. ከአዋሳ

    ReplyDelete